19. ከሰማይ ንስሮች ይልቅ፣ጠላቶቻችን ፈጣኖች ናቸው፤በተራሮች ላይ አሳደዱን፤በምድረ በዳም ሸመቁብን።
20. በእግዚአብሔር የተቀባው፣ የሕይወታችን እስትንፋስ፣በወጥመዳቸው ተያዘ፤በጥላው ሥር፣በአሕዛብ መካከል እንኖራለን ብለን አስበን ነበር።
21. አንቺ በዖፅ ምድር የምትኖሪ፣የኤዶምያስ ሴት ልጅ ሆይ፤ ደስ ይበልሽ፤ ሐሴትም አድርጊነገር ግን ለአንቺም ደግሞ ጽዋው ይደርስሻል፤ትሰክሪያለሽ፤ ዕርቃንሽንም ትጋለጫለሽ።