51. በከተማዬ ባሉት ሴቶች ሁሉ ላይ የደረሰውን ማየቴ፣ነፍሴን አስጨነቃት።
52. ያለ ምክንያት ጠላቶቼ የሆኑ፣እንደ ወፍ አደኑኝ።
53. ሕይወቴን በጒድጓድ ውስጥ ሊያጠፉ ሞከሩ፣ድንጋይም በላዬ አደረጉ።
54. ውሃ ሞልቶ በዐናቴ ላይ ፈሰሰ፤ጠፍቻለሁ ብዬ አሰብሁ።
55. በጥልቁ ጒድጓድ ውስጥ ሳለሁ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንተን ስም ጠራሁ።
56. ልመናዬን ሰምተሃል፤ “ርዳታም ፈልጌ ስጮኽ፣ከመስማት ጆሮህን አትከልክል።”
57. በጠራሁህ ጊዜ ቀረብኸኝ፣እንዲሁም፣ “አትፍራ” አልኸኝ።
58. ጌታ ሆይ፤ ለእኔ ተሟገትኽልኝ፤ሕይወቴንም ተቤዠህ።
59. እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኔ ላይ የተደረገውን ግፍ አየህ፤ፍርዴን ፍረድልኝ!
60. በቀላቸውን ሁሉ፣በእኔም ላይ ያሰቡትን ዐድማ አየህ።
61. እግዚአብሔር ሆይ፤ ስድባቸውን ሁሉ፣በእኔ ላይ ያሰቡትን ዐድማ ሁሉ ሰማህ፤
62. ይህም ቀኑን ሙሉ በእኔ ላይ፣ጠላቶቼ የሚያውጠነጥኑትና የሚያንሾካሹኩት ነው።
63. ተመልከታቸው! ቆመውም ሆነ ተቀምጠው፣በዘፈናቸው ይሣለቁብኛል።
64. እግዚአብሔር ሆይ፤ እጆቻቸው ላደረጉት፣የሚገባውን መልሰህ ክፈላቸው።
65. በልባቸው ላይ መጋረጃን ዘርጋ፤ርግማንህም በላያቸው ይሁን!