ሰቆቃወ 3:43-57 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

43. “ራስህን በቊጣ ከደንህ፤ አሳደድኸንም፤ያለ ርኅራኄም ገደልኸን።

44. ጸሎት እንዳያልፍ፣ራስህን በደመና ሸፈንህ።

45. በአሕዛብ መካከል፣አተላና ጥራጊ አደረግኸን።

46. “ጠላቶቻችን ሁሉ፣አፋቸውን በእኛ ላይ ከፈቱ።

47. በጥፋትና በመፈራረስ፣በችግርና በሽብር ተሠቃየን።

48. የእንባ ጐርፍ ከዐይኔ ፈሰሰ፤ሕዝቤ አልቋልና።

49. ያለ ዕረፍት፣ያለ ማቋረጥ ዐይኖቼ እንባ ያፈሳሉ፤

50. እግዚአብሔር ከላይ፣ከሰማይ እስኪያይ ድረስ።

51. በከተማዬ ባሉት ሴቶች ሁሉ ላይ የደረሰውን ማየቴ፣ነፍሴን አስጨነቃት።

52. ያለ ምክንያት ጠላቶቼ የሆኑ፣እንደ ወፍ አደኑኝ።

53. ሕይወቴን በጒድጓድ ውስጥ ሊያጠፉ ሞከሩ፣ድንጋይም በላዬ አደረጉ።

54. ውሃ ሞልቶ በዐናቴ ላይ ፈሰሰ፤ጠፍቻለሁ ብዬ አሰብሁ።

55. በጥልቁ ጒድጓድ ውስጥ ሳለሁ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንተን ስም ጠራሁ።

56. ልመናዬን ሰምተሃል፤ “ርዳታም ፈልጌ ስጮኽ፣ከመስማት ጆሮህን አትከልክል።”

57. በጠራሁህ ጊዜ ቀረብኸኝ፣እንዲሁም፣ “አትፍራ” አልኸኝ።

ሰቆቃወ 3