ሰቆቃወ 3:43-52 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

43. “ራስህን በቊጣ ከደንህ፤ አሳደድኸንም፤ያለ ርኅራኄም ገደልኸን።

44. ጸሎት እንዳያልፍ፣ራስህን በደመና ሸፈንህ።

45. በአሕዛብ መካከል፣አተላና ጥራጊ አደረግኸን።

46. “ጠላቶቻችን ሁሉ፣አፋቸውን በእኛ ላይ ከፈቱ።

47. በጥፋትና በመፈራረስ፣በችግርና በሽብር ተሠቃየን።

48. የእንባ ጐርፍ ከዐይኔ ፈሰሰ፤ሕዝቤ አልቋልና።

49. ያለ ዕረፍት፣ያለ ማቋረጥ ዐይኖቼ እንባ ያፈሳሉ፤

50. እግዚአብሔር ከላይ፣ከሰማይ እስኪያይ ድረስ።

51. በከተማዬ ባሉት ሴቶች ሁሉ ላይ የደረሰውን ማየቴ፣ነፍሴን አስጨነቃት።

52. ያለ ምክንያት ጠላቶቼ የሆኑ፣እንደ ወፍ አደኑኝ።

ሰቆቃወ 3