ሰቆቃወ 3:34-37 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. የምድሪቱ እስረኞች ሁሉ፣በእግር ሲረገጡ፣

35. በልዑል ፊት፣ሰው መብቱ ሲነፈገው፣

36. ሰው ፍትሕ ሲጓደልበት፣ጌታ እንዲህ ዐይነቱን ነገር አያይምን?

37. እግዚአብሔር ካላዘዘ በቀር፤ተናግሮ መፈጸም የሚችል ማን ነው?

ሰቆቃወ 3