ሰቆቃወ 3:33-44 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

33. ሆን ብሎ ችግርን፣ወይም መከራን በሰው ልጆች ላይ አያመጣምና።

34. የምድሪቱ እስረኞች ሁሉ፣በእግር ሲረገጡ፣

35. በልዑል ፊት፣ሰው መብቱ ሲነፈገው፣

36. ሰው ፍትሕ ሲጓደልበት፣ጌታ እንዲህ ዐይነቱን ነገር አያይምን?

37. እግዚአብሔር ካላዘዘ በቀር፤ተናግሮ መፈጸም የሚችል ማን ነው?

38. ክፉም ሆነ መልካም ነገር፣ከልዑል አፍ የሚወጣ አይደለምን?

39. ታዲያ ሕያው ሰው በኀጢአቱ ሲቀጣ፣ስለ ምን ያጒረመርማል?

40. መንገዳችንን እንመርምር፤ እንፈትን፤ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ።

41. ልባችንን ከእጃችን ጋር በሰማይ ወዳለው ወደ አምላካችንእናንሣ፤ እንዲህም እንበል፤

42. “ዐምፀናል፤ ኀጢአትም ሠርተናል፤አንተም ይቅር አላልኸንም።

43. “ራስህን በቊጣ ከደንህ፤ አሳደድኸንም፤ያለ ርኅራኄም ገደልኸን።

44. ጸሎት እንዳያልፍ፣ራስህን በደመና ሸፈንህ።

ሰቆቃወ 3