ሰቆቃወ 3:29-37 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. ፊቱን በዐቧራ ውስጥ ይቅበር፤ተስፋ ሊኖር ይችላልና።

30. ጒንጩን ለሚመታው ሰው ይስጥ፤ውርደትንም ይጥገብ።

31. እግዚአብሔር ሰውን፣ለዘላለም አይጥልምና፤

32. መከራን ቢያመጣ እንኳ ይራራል፤ታላቅ ፍቅሩ አይለወጥምና

33. ሆን ብሎ ችግርን፣ወይም መከራን በሰው ልጆች ላይ አያመጣምና።

34. የምድሪቱ እስረኞች ሁሉ፣በእግር ሲረገጡ፣

35. በልዑል ፊት፣ሰው መብቱ ሲነፈገው፣

36. ሰው ፍትሕ ሲጓደልበት፣ጌታ እንዲህ ዐይነቱን ነገር አያይምን?

37. እግዚአብሔር ካላዘዘ በቀር፤ተናግሮ መፈጸም የሚችል ማን ነው?

ሰቆቃወ 3