19. የጭንቀቴንና የመንከራተቴን፣ምሬትንና ሐሞትን አስባለሁ።
20. ዘወትር አስበዋለሁ፤ነፍሴም በውስጤ ተዋርዳለች።
21. ሆኖም ይህን አስባለሁእንግዲያስ ተስፋ አለኝ፤
22. ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር የተነሣ ነው፤ርኅራኄው አያልቅምና።
23. ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ታማኝነትህም ብዙ ነው።
24. ራሴን እንዲህ አልሁት፤ “እግዚአብሔር ዕድል ፈንታዬ ነው፤ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ።
25. እርሱን ተስፋ ለሚያደርጉት፣ለሚፈልገውም ሰው እግዚአብሔር መልካም ነው።
26. ሰው የእግዚአብሔርን ማዳን፣ዝም ብሎ ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።
27. ሰው በወጣትነቱ፣ቀንበር ቢሸከም መልካም ነው።
28. ብቻውን ዝም ብሎ ይቀመጥ፤ እግዚአብሔር አሸክሞታልና።
29. ፊቱን በዐቧራ ውስጥ ይቅበር፤ተስፋ ሊኖር ይችላልና።
30. ጒንጩን ለሚመታው ሰው ይስጥ፤ውርደትንም ይጥገብ።