ሰቆቃወ 1:20-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. “አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዴት ተጨንቄአለሁ!በውስጤ ተሠቃይቼአለሁ፤በልቤ ታውኬአለሁ፤እጅግ ዐመፀኛ ሆኛለሁና፤በውጭ ሰይፍ ይፈጃል፤በቤትም ውስጥ ሞት አለ።

21. “ሰዎች የሥቃይ ልቅሶዬን ሰሙ፤የሚያጽናናኝ ግን ማንም የለም፤ጠላቶቼ ሁሉ ጭንቀቴን ሰሙ፤አንተ ባደረግኸውም ደስ አላቸው፤አቤቱ የተናገርኻት ቀን ትምጣ፤እነርሱም እንደ እኔ ይሁኑ።

ሰቆቃወ 1