ራእይ 19:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “ከዚህ በኋላ የብዙ ሰዎችን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ በሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ሃሌ ሉያ!ማዳን፣ ክብርና ኀይል የአምላካችን ነው፤

2. ፍርዱ እውነትና ጽድቅ ነውና፤በዝሙቷ ምድርን ያረከሰችውን፣ታላቂቱን አመንዝራ ፈርዶባታል፤ስለ አገልጋዮቹም ደም ተበቅሏታል።”

3. ደግሞም እንዲህ አሉ፤“ሃሌ ሉያ!ጢስ ከእርሷ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል።”

4. ሃያ አራቱ ሽማግሌዎችና አራቱ ሕያዋን ፍጡራን በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው አምላክ ወድቀው ሰገዱ፤ እንዲህም አሉ፤“አሜን፣ ሃሌ ሉያ!”

ራእይ 19