30. በዚያን ጊዜ ከጐኑ ዋና ባለ ሙያ ነበርሁ።ሁል ጊዜ በፊቱ ሐሤት እያደረግሁ፣ዕለት ተዕለት በደስታ እሞላ ነበር፤
31. የእርሱ በሆነው መላው ዓለም ሐሤት እያደረግሁ፣በሰው ልጆች ደስ እሰኝ ነበር።
32. “እንግዲህ፣ ልጆቼ ሆይ፤ አድምጡኝ፤መንገዴን የሚጠብቁ ቡሩካን ናቸው።
33. ምክሬን አድምጡ፤ ጥበበኞች ሁኑ፤ቸልም አትበሉት።
34. በየለቱ ደጃፌ ላይ የሚጠብቅ፣በበራፌ ላይ የሚጠባበቅ፣የሚያዳምጠኝ ሰው ቡሩክ ነው።
35. የሚያገኘኝ ሁሉ ሕይወትን ያገኛልና፤ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን ይቀበላል።
36. የሚያጣኝ ሁሉ ግን ራሱ ይጐዳል፤የሚጠሉኝም ሁሉ ሞትን ይወዳሉ።