ምሳሌ 27:7-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ለጠገበ ማር አይጥመውም፤ለተራበ ግን እሬት እንኳ ይጣፍጠዋል።

8. ከቤቱ ወጥቶ የሚባዝን ሰው፣ጎጆዋን ለቃ እንደምትባዝን ወፍ ነው።

9. ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤የወዳጅ ማስደሰትም ከቅን ምክሩ ይመነጫል።

10. የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ አትተው፤መከራ በሚያጋጥምህ ጊዜ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፤ሩቅ ካለ ወንድም ቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል።

11. ልጄ ሆይ፤ ጠቢብ ሁን፤ ልቤን ደስ አሰኘው፤ለሚንቁኝ ሁሉ መልስ መስጠት እችል ዘንድ።

12. ጥንቁቅ አደጋን አይቶ ይሸሸጋል፤ማስተዋል የጐደለው ግን ወደዚያው ይሄዳል፤ ይጐዳልም።

13. ለማይታወቅ ሰው የተዋሰን ልብሱን ግፈፈው፤ለዘልዛላ ሴት ከተዋሰማ አግተው።

14. ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ ባልንጀራውን በማለዳ ቢመርቅ፣እንደ ርግማን ይቈጠራል።

15. ጨቅጫቃ ሚስት፣ በዝናብ ቀን እንደሚወርድ የማያቋርጥጠፈጠፍ ናት፤

16. እርሷን ለመግታት መሞከር፣ ነፋስን እንደ መግታት ወይም ዘይትንበእጅ እንደ መጨበጥ ነው።

17. ብረት ብረትን እንደሚስል፣ሰውም ሌላውን ሰው እንደዚሁ ይስለዋል።

18. በለስን የሚንከባከብ ፍሬዋን ይበላል፤ጌታውን የሚያገለግልም ክብርን ይጐናጸፋል።

ምሳሌ 27