1. የልብ ዕቅድ የሰው ነው፤የአንደበት መልስ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
2. ለሰው መንገዱ ሁሉ ንጹሕ መስሎ ይታየዋል፤መነሻ ሐሳቡ ግን በእግዚአብሔር ይመዘናል።
3. የምታደርገውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤ዕቅድህም ሁሉ ይሳካልሃል።
4. እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ለራሱ ዐላማ ሠርቶአል፤ክፉዎችንም እንኳ ለጥፋት ቀን አዘጋጅቶአል።
5. እግዚአብሔር በልብ የሚታበዩትን ሁሉ ይጸየፋል፤እነርሱም ከቅጣት እንደማያመልጡ በርግጥ ዕወቅ።
6. በፍቅርና በታማኝነት ኀጢአት ይሰረያል፤ እግዚአብሔርን በመፍራት ሰው ከክፋት ይርቃል።
7. የሰው መንገድ እግዚአብሔርን ደስ ሲያሰኘው፣ጠላቶቹ እንኳ አብረውት በሰላም እንዲኖሩ ያደርጋል።