መዝሙር 98:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ውዳሴን አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፤

5. ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት፤በበገናና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩለት፤

6. በእንቢልታና በመለከት ድምፅ፣በንጉሡ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ።

7. ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ፣ዓለምና የሚኖሩባትም ሁሉ ያስገምግሙ።

8. ወንዞች በእጃቸው ያጨብጭቡ፤ተራሮችም በአንድነት ይዘምሩ፤

መዝሙር 98