መዝሙር 96:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ ዘምሩ፤ምድር ሁሉ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።

2. ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ስሙንም ባርኩ፤ማዳኑንም ነጋ ጠባ አውሩ።

3. ክብሩን በሕዝቦች መካከል፣ድንቅ ሥራውንም በሰዎች ሁሉ ፊት ተናገሩ።

4. እግዚአብሔር ታላቅ ነውና፤ ውዳሴም የሚገባው ነው፤ከአማልክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ ይገባዋል።

5. የሕዝብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።

መዝሙር 96