መዝሙር 92:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ደነዝ ሰው ይህን አያውቅም፤ነኁላላም አያስተውለውም።

7. ክፉዎች እንደ ሣር ቢበቅሉ፣ክፉ አድራጊዎች ቢለመልሙ፣ለዘላለሙ ይጠፋሉ፤

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም ልዑል ነህ።

9. ጠላቶችህ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ይጠፋሉና፤ክፉ አድራጊዎችም ሁሉ ይበተናሉ።

10. የእኔን ቀንድ ግን እንደ አውራሪስ ቀንድ ከፍ ከፍ አደረግኸው፤በለጋ ዘይትም አረሰረስኸኝ።

11. ዐይኖቼ የባላንጦቼን ውድቀት አዩ፤ጆሮዎቼም የክፉ ጠላቶቼን ድቀት ሰሙ።

መዝሙር 92