መዝሙር 92:3-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ዐሥር አውታር ባለው በገና፣በመሰንቆም ቅኝት ታጅቦ ማወጅ ጥሩ ነው።

4. እግዚአብሔር ሆይ፤ በሥራህ ስለ ተደሰትሁ፣ስለ እጅህ ሥራ በደስታ እዘምራለሁ።

5. እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ታላቅ ነው!ሐሳብህስ ምን ያህል ጥልቅ ነው!

6. ደነዝ ሰው ይህን አያውቅም፤ነኁላላም አያስተውለውም።

7. ክፉዎች እንደ ሣር ቢበቅሉ፣ክፉ አድራጊዎች ቢለመልሙ፣ለዘላለሙ ይጠፋሉ፤

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም ልዑል ነህ።

9. ጠላቶችህ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ይጠፋሉና፤ክፉ አድራጊዎችም ሁሉ ይበተናሉ።

10. የእኔን ቀንድ ግን እንደ አውራሪስ ቀንድ ከፍ ከፍ አደረግኸው፤በለጋ ዘይትም አረሰረስኸኝ።

11. ዐይኖቼ የባላንጦቼን ውድቀት አዩ፤ጆሮዎቼም የክፉ ጠላቶቼን ድቀት ሰሙ።

መዝሙር 92