7. በአጠገብህ ሺህ፣ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃል፤ወደ አንተ ግን አይቀርብም።
8. በዐይንህ ብቻ ትመለከታለህ፤የክፉዎችንም መቀጣት ታያለህ።
9. እግዚአብሔርን መሸሸጊያ፣ልዑልንም መጠጊያህ አድርገኸዋልና።
10. ክፉ ነገር አያገኝህም፤መቅሠፍትም ወደ ድንኳንህ አይገባም፤
11. በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ፣መላእክቱን ስለ አንተ ያዛቸዋልና።
12. እግርህ ከድንጋይ ጋር እንዳይጋጭ፣በእጆቻቸው ወደ ላይ ያነሡሃል።
13. በአንበሳና በእፉኝት ላይ ትጫማለህ፤ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ።