መዝሙር 91:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. እግርህ ከድንጋይ ጋር እንዳይጋጭ፣በእጆቻቸው ወደ ላይ ያነሡሃል።

13. በአንበሳና በእፉኝት ላይ ትጫማለህ፤ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ።

14. “ወዶኛልና እታደገዋለሁ፤ስሜን አውቆአልና እከልለዋለሁ።

15. ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤በመከራው ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ።

16. ረጅም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤ማዳኔንም አሳየዋለሁ።”

መዝሙር 91