መዝሙር 9:2-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤ልዑል ሆይ፤ ስምህን በመዝሙር እወድሳለሁ።

3. ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ ጊዜ፣ተሰነካክለው ከፊትህ ይጠፋሉ፤

4. ፍርዴም ጒዳዬም በአንተ እጅ ናቸውና፤ቅን ፍርድ እየሰጠህ በዙፋንህ ላይ ተቀምጠሃል።

5. ሕዝቦችን ገሠጽህ፤ ክፉዎችንም አጠፋህ፤ስማቸውንም እስከ ወዲያኛው ደመሰስህ።

6. ጠላቶች ለዘላለም ጠፉ፤ከተሞቻቸውንም ገለባበጥሃቸው፤መታሰቢያቸውም ተደምስሶአል።

7. እግዚአብሔር ግን ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ነው፤መንበሩንም ለፍርድ አጽንቶአል።

8. ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል፤ሕዝቦችንም በፍትሕ ይገዛል።

መዝሙር 9