መዝሙር 9:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ሥራውንም በሕዝቦች መካከል በግልጽ አውሩ፤

12. ደም ተበቃዩ ዐስቦአቸዋልና፤የጭቍኖችንም ጩኸት አልዘነጋም።

13. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ የሚያደርሱብኝን መከራ ተመልከት፤አይተህም ራራልኝ፤ ከሞት ደጅም አንሥተህ መልሰኝ፤

14. ይህን ስታደርግልኝ፣ በጽዮን ሴት ልጅ ደጅ፣ምስጋናህን ዐውጃለሁ፤በማዳንህም ሐሤት አደርጋለሁ።

15. አሕዛብ በቈፈሩት ጒድጓድ ገቡ፤እግራቸውም ራሳቸው በስውር ባስቀመጡት ወጥመድ ተያዘ።

መዝሙር 9