1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምድርህ በጎ ውለሃል፤የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ።
2. የሕዝብህን በደል ይቅር አልህ፤ኀጢአታቸውንም ሁሉ ሸፈንህ። ሴላ
3. መዓትህን ሁሉ አራቅህ፤ከብርቱ ቍጣህም ተመለስህ።
4. መድኀኒታችን የሆንህ አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤በእኛ ላይ የተቃጣውን ቍጣህን መልሰው።
5. የምትቈጣን ለዘላለም ነውን?ቊጣህስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይቀጥላልን?
6. ሕዝብህ በአንተ ሐሤት ያደርግ ዘንድ፣መልሰህ ሕያዋን አታደርገንምን?
7. እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አሳየን፤ማዳንህን ለግሰን።
8. እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤ለሕዝቡ፣ ለቅዱሳኑ ሰላምን ይናገራልና፤ዳሩ ግን ወደ ከንቱ ምግባራቸው አይመለሱ።