መዝሙር 80:3-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤እንድንም ዘንድ፣ፊትህን አብራልን።

4. የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤በሕዝብህ ጸሎት ላይ ቍጣህ የሚነደው፣እስከ መቼ ድረስ ነው?

5. የእንባ እንጀራ አበላሃቸው፤ስፍር የሞላ እንባም አጠጣሃቸው።

6. ለጎረቤቶቻችን የጠብ ምክንያት አደረግኸን፤ጠላቶቻችንም ተሣሣቁብን።

7. የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤እንድንም ዘንድ፣ፊትህን አብራልን።

8. ከግብፅ የወይን ግንድ አመጣህ፤አሕዛብን አባርረህ እርሷን ተከልሃት።

9. መሬቱን መነጠርህላት፤እርሷም ሥር ሰዳ አገሩን ሞላች።

10. ተራሮች በጥላዋ ተሸፈኑ፤ግዙፍ ዝግቦችም በቅርንጫፎቿ ተጠለሉ።

11. ቅርንጫፎቿን እስከ ባሕሩ፣ቊጥቋጦዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች።

መዝሙር 80