1. ዮሴፍን እንደ በግ መንጋ የምትመራ፣የእስራኤል እረኛ ሆይ፤ ስማን፤በኪሩቤል ላይ በዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፤በብርሃንህ ተገለጥ፤
2. በኤፍሬም፣ በብንያምና በምናሴ ፊት ደምቀህ ታይ።ኀይልህን አንቀሳቅስ፤መጥተህም አድነን።
3. አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤እንድንም ዘንድ፣ፊትህን አብራልን።
4. የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤በሕዝብህ ጸሎት ላይ ቍጣህ የሚነደው፣እስከ መቼ ድረስ ነው?
5. የእንባ እንጀራ አበላሃቸው፤ስፍር የሞላ እንባም አጠጣሃቸው።