መዝሙር 8:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው!ክብርህ ከሰማያት በላይ፣ከፍ ከፍ ብሎአል።

2. ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ ሕፃናት አፍ፣ምስጋናን አዘጋጀህ፤ከጠላትህ የተነሣ፣ባላንጣንና ቂመኛን ጸጥ ታሰኝ ዘንድ።

3. የጣቶችህን ሥራ፣ሰማያትህን ስመለከት፣በስፍራቸው ያኖርሃቸውን፣ጨረቃንና ከዋክብትን ሳይ፣

መዝሙር 8