መዝሙር 78:66-72 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

66. ጠላቶቹን መትቶ ወደ ኋላ መለሳቸው፤የዘላለም ውርደትም አከናነባቸው።

67. የዮሴፍን ድንኳን ተዋት፤የኤፍሬምንም ነገድ አልመረጠም።

68. ነገር ግን የይሁዳን ነገድ፣የወደዳትን የጽዮንን ተራራ መረጠ።

69. መቅደሱን እንደ ታላቅ ከፍታ፣ለዘላለም እንደ መሠረታት ምድር ሠራት።

70. ባሪያውን ዳዊትን መረጠ፤ከበጎች ጒረኖ ውስጥ ወሰደው፤

71. ለሕዝቡ ለያዕቆብ፣ለርስቱም ለእስራኤል እረኛ ይሆን ዘንድ፣የሚያጠቡ በጎችን ከመከተል አመጣው።

72. እርሱም በቅን ልቡ ጠበቃቸው፤ብልኀት በተሞላ እጁም መራቸው።

መዝሙር 78