መዝሙር 78:47-50 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

47. የወይን ተክላቸውን በበረዶ፣የበለስ ዛፋቸውንም በውርጭ አጠፋ።

48. ከብቶቻቸውን ለበረዶ፣የከብት መንጋቸውን ለመብረቅ እሳት ዳረገ።

49. ጽኑ ቍጣውን በላያቸው ሰደደ፤መዓቱን፣ የቅናቱን ቍጣናመቅሠፍቱን ላከባቸው፤አጥፊ የመላእክት ሰራዊትም ሰደደባቸው።

50. ለቊጣው መንገድ አዘጋጀ፤ነፍሳቸውንም ከሞት አላተረፈም፤ነገር ግን ሕይወታቸውን ለመቅሠፍት አሳልፎ ሰጠ።

መዝሙር 78