መዝሙር 78:41-43 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

41. ደግመው ደጋግመው እግዚአብሔርን ተፈታተኑት፤የእስራኤልንም ቅዱስ አስቈጡት።

42. እነርሱን በዚያን ቀን ከጠላት የታደገበትን፣ያን ኀይሉን አላስታወሱም፤

43. በግብፅ ያደረገውን ታምራዊ ምልክት፣በጣኔዎስም በረሓ ያሳየውን ድንቅ ሥራ አላሰቡም።

መዝሙር 78