4. እኛም ከልጆቻቸው አንደብቀውም፤ የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ኀይሉንና ያደረገውን ድንቅ ሥራ፣ለሚቀጥለው ትውልድ እንናገራለን።
5. ለያዕቆብ ሥርዐትን መሠረተ፤በእስራኤልም ሕግን ደነገገ፤ልጆቻቸውንም እንዲያስተምሩ፣አባቶቻችንን አዘዘ።
6. ይህም የሚቀጥለው ትውልድ እንዲያውቅ፣እነርሱም በተራቸው ለልጆቻቸው፣ገና ለሚወለዱት እንዲነግሩ ነው።
7. እነርሱም በእግዚአብሔር ይታመናሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ አይረሱም፤ትእዛዞቹንም ይጠብቃሉ።