መዝሙር 78:31-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

31. የእግዚአብሔር ቊጣ በላያቸው ላይ መጣ፤ከመካከላቸውም ብርቱ ነን ባዮችን ገደለ፤የእስራኤልንም አበባ ወጣቶች ቀጠፈ።

32. ይህም ሁሉ ሆኖ በበደላቸው ገፉበት፤ድንቅ ሥራዎቹንም አላመኑም።

33. ስለዚህ ዘመናቸውን በከንቱ፣ዕድሜአቸውንም በድንጋጤ ጨረሰ።

መዝሙር 78