28. በሰፈራቸውም ውስጥ፣በድንኳናቸው ዙሪያ አወረደ።
29. እነርሱም እስኪጠግቡ ድረስ በሉ፤እጅግ የጐመጁትን ሰጥቶአቸዋልና።
30. ነገር ግን ገና ምኞታቸውን ሳያረኩ፣ምግቡ ገና በአፋቸው ውስጥ እያለ፣
31. የእግዚአብሔር ቊጣ በላያቸው ላይ መጣ፤ከመካከላቸውም ብርቱ ነን ባዮችን ገደለ፤የእስራኤልንም አበባ ወጣቶች ቀጠፈ።
32. ይህም ሁሉ ሆኖ በበደላቸው ገፉበት፤ድንቅ ሥራዎቹንም አላመኑም።
33. ስለዚህ ዘመናቸውን በከንቱ፣ዕድሜአቸውንም በድንጋጤ ጨረሰ።
34. እርሱ በገደላቸው ጊዜ ፈለጉት፤ከልባቸው በመሻትም ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ።
35. እግዚአብሔር ዐለታቸው፣ልዑል አምላክ ቤዛቸው እንደሆነ አሰቡ።
36. ነገር ግን በአፋቸው ሸነገሉት፤በአንደበታቸው ዋሹት።
37. ልባቸው በእርሱ የጸና አልነበረም፤ለኪዳኑም ታማኞች አልነበሩም።
38. እርሱ ግን መሓሪ እንደ መሆኑ፣በደላቸውን ይቅር አለ፤አላጠፋቸውም፤ቊጣውን ብዙ ጊዜ ገታ፤መዓቱንም ሁሉ አላወረደም።