መዝሙር 78:25-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. ሰዎች የመላእክትን እንጀራ በሉ፤ጠግበው እስከሚተርፍ ድረስ ምግብ ላከላቸው።

26. የምሥራቁን ነፋስ ከሰማይ አስነሣ፤የደቡብንም ነፋስ በኀይሉ አመጣ።

27. ሥጋን እንደ ዐፈር፣የሚበሩትን ወፎች እንደ ባሕር አሸዋ አዘነበላቸው፤

28. በሰፈራቸውም ውስጥ፣በድንኳናቸው ዙሪያ አወረደ።

29. እነርሱም እስኪጠግቡ ድረስ በሉ፤እጅግ የጐመጁትን ሰጥቶአቸዋልና።

30. ነገር ግን ገና ምኞታቸውን ሳያረኩ፣ምግቡ ገና በአፋቸው ውስጥ እያለ፣

መዝሙር 78