መዝሙር 78:14-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ቀን በደመና መራቸው፤ሌሊቱንም ሁሉ በእሳት ብርሃን።

15. ዐለቱን በምድረ በዳ ሰነጠቀ፤እንደ ባሕር የበዛ ውሃ አጠጣቸው፤

16. ምንጭ ከቋጥኝ አፈለቀ፤ውሃን እንደ ወንዝ አወረደ።

17. እነርሱ ግን በምድረ በዳ በልዑል ላይ በማመፅ፣በእርሱ ላይ ኀጢአት መሥራታቸውን ቀጠሉ።

18. እጅግ የተመኙትን ምግብ በመጠየቅ፣እግዚአብሔርን በልባቸው ተፈታተኑት።

19. እንዲህም ብለው በእግዚአብሔር ላይ ተናገሩ፤“እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማዕድ ማሰናዳት ይችላልን?

መዝሙር 78