መዝሙር 7:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ክፋትን እያማጠ ያለ ሰው፣ቅጥፈትን አርግዞ፣ ሐሰትን ይወልዳል።

15. ጒድጓድ ምሶ ዐፈሩን የሚያወጣ፣ባዘጋጀው ጒድጓድ ራሱ ይገባበታል።

16. ተንኰሉ ወደ ራሱ ይመለሳል፤ዐመፃውም በገዛ ዐናቱ ላይ ይወርዳል።

17. ስለ ጽድቁ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀርባለሁ፤የልዑል እግዚአብሔርን ስም በመዝሙር አወድሳለሁ።

መዝሙር 7