መዝሙር 63:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ነፍሴ አንተን የሙጥኝ ብላለች፤ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች።

9. ነፍሴን ለማጥፋት የሚሹ ግን፣ወደ ምድር ጥልቅ ይወርዳሉ፤

10. ለሰይፍ አልፈው ይሰጣሉ፤የቀበሮዎችም ምግብ ይሆናሉ።

11. ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፤በእግዚአብሔርም ስም ቃል የሚገቡ ሁሉ ይከብራሉ፤የሐሰተኞች አንደበትም ትዘጋለች።

መዝሙር 63