መዝሙር 51:2-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. በደሌን ፈጽሞ እጠብልኝ፤ከኀጢአቴም አንጻኝ።

3. እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፤ኀጢአቴም ዘወትር በፊቴ ነው።

4. በውሳኔህ ትክክል፣በምትሰጠው ፍርድም ንጹሕ ትሆን ዘንድ፣አንተን፣ በእርግጥ አንተን ብቻ በደልሁ፤በፊትህም ክፉ ነገር አደረግሁ።

5. ስወለድ ጀምሮ በደለኛ፣ገና እናቴም ስትፀንሰኝ ኀጢአተኛ ነኝ።

6. እነሆ፤ እውነትን ከሰው ልብ ትሻለህ፤ስለዚህ ጥልቅ ጥበብን በውስጤ አስተምረኝ።

7. በሂሶጵ እርጨኝ፤ እኔም እነጻለሁ፤እጠበኝ፤ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።

8. ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፤ያደቀቅሃቸው ዐጥንቶቼም ደስ ይበላቸው።

9. ፊትህን ከኀጢአቴ መልስ፤በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።

10. አምላኬ ሆይ፤ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።

11. ከፊትህ አትጣለኝ፤ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድ።

መዝሙር 51