መዝሙር 50:21-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. ይህን አድርገህ ዝም አልሁ፤እንዳንተ የሆንሁ መሰለህ።አሁን ግን እገሥጽሃለሁ፣ፊት ለፊትም እወቅስሃለሁ።

22. “እናንተ እግዚአብሔርን የምትረሱ፤ ይህን ልብ በሉ፤አለበለዚያ ብትንትናችሁን አወጣለሁ፤የሚያድናችሁም የለም።

23. የምስጋናን መሥዋዕት የሚሠዋ ያከብረኛል፤መንገዱንም ቀና ለሚያደርግ፣የእግዚአብሔርን ማዳን አሳየዋለሁ።”

መዝሙር 50