መዝሙር 49:4-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፤እንቆቅልሼንም በበገና እፈታለሁ።

5. የአጭበርባሪዎች ክፋት በከበበኝ ጊዜ፣በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ?

6. በሀብታቸው የሚመኩትን፣በብልጽግናቸውም የሚታመኑትን ለምን እፈራለሁ?

7. የሌላውን ሕይወት መቤዠት የሚችል ሰው፣ወይም ለእግዚአብሔር ወጆ የሚከፍልለት ማንም የለም።

8. የነፍስ ቤዛ ውድ ነውና፤በቂ ዋጋም ከቶ ሊገኝለት አይችልም፤

9. በዚህም ዘላለም ይኖራል፣መበስበስንም አያይም።

10. ጠቢባን ሟች መሆናቸው የሚታይ ነው፤ቂልና ሞኝም በአንድነት ይጠፋሉ፤ጥሪታቸውንም ለሌላው ጥለው ይሄዳሉ።

መዝሙር 49