14. እንደ በጎች ለሲኦል የተዳረጉ ናቸው፤ሞትም እረኛቸው ይሆናል፤ቅኖች በማለዳ ይገዟቸዋል፤አካላቸው ከክብር ቤታቸው ርቆ፣በሲኦል ይፈራርሳል።
15. እግዚአብሔር ግን ነፍሴን ከሲኦል እጅ ይቤዣታል፤በርግጥም በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት አለኝ። ሴላ
16. ሰው ባለጠጋ ሲሆን፣የቤቱም ክብር ሲበዛለት አትፍራ፤
17. በሚሞትበትም ጊዜ ይዞት የሚሄደው አንዳች የለምና፤ክብሩም አብሮት አይወርድም።
18. በሕይወት ሳለ ራሱን እንደ ተባረከ ቢቈጥርም፣ሰዎች በበለጸግህ ጊዜ ቢያወድሱህም፣
19. ብርሃን ከቶ ወደማያዩት፣ወደ አባቶች ማኅበር ይቀላቀላል።
20. ሰው በሀብቱ እንደ ተከበረ አይዘልቅም፤ታይተው የሚጠፉ እንስሳትን ይመስላል።