መዝሙር 49:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እናንተ ሕዝቦች ሁላችሁ፤ ይህን ስሙ፤በዓለም የምትኖሩ ሁሉ፤ ይህን አድምጡ።

2. ዝቅተኞችና ከፍተኞች፤ባለጠጎችና ድኾች ይህን በአንድነት ስሙ።

3. አፌ የጥበብን ቃል ይናገራል፤የልቤም ሐሳብ ማስተዋልን ይሰጣል።

4. ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፤እንቆቅልሼንም በበገና እፈታለሁ።

መዝሙር 49