መዝሙር 47:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. አምላክ በእልልታ፣ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።

6. አምላካችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤ንጉሣችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤

7. እግዚአብሔር የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ምርጥ ዝማሬ አቅርቡለት።

8. እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ነግሦአል፤እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦአል።

9. ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋር፣የሕዝቦች መኳንንት ተሰበሰቡ፤የምድር ነገሥታት የእግዚአብሔር ናቸውና፤እርሱም እጅግ ከፍ ከፍ ያለ ነው።

መዝሙር 47