መዝሙር 47:3-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ሕዝቦችን ከእኛ በታች አደረገ፤መንግሥታትንም ከእግራችን ሥር አስገዛልን።

4. ለሚወደው ለያዕቆብ ክብር የሆነችውን፣ርስታችንን እርሱ መረጠልን። ሴላ

5. አምላክ በእልልታ፣ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።

6. አምላካችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤ንጉሣችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤

7. እግዚአብሔር የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ምርጥ ዝማሬ አቅርቡለት።

8. እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ነግሦአል፤እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦአል።

መዝሙር 47