መዝሙር 40:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አትንፈገኝ፤ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ፤

12. ስፍር ቍጥር የሌለው ክፋት ከቦኛልና፤የኀጢአቴ ብዛት ስለ ያዘኝ ማየት ተስኖኛል፤ከራሴ ጠጒር ይልቅ በዝቶአል፤ልቤም ከድቶኛል።

13. እግዚአብሔር ሆይ፤ ታድነኝ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።

14. ነፍሴን ለመንጠቅ የሚፈልጉ፣ይፈሩ፤ ይዋረዱም፤ጒዳቴንም የሚሹ፣ተዋርደው በመጡበት ይመለሱ።

መዝሙር 40