መዝሙር 39:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እኔ፣ “በአንደበቴ እንዳልበድል፣መንገዴን እጠብቃለሁ፤ክፉዎችም በእኔ ዘንድ እስካሉ ድረስ፣ልጓም በአፌ አስገባለሁ” አልሁ።

2. እንደ ዲዳ ዝም አልሁ፤ለበጎ ነገር እንኳ አፌን ዘጋሁ፤ሆኖም ጭንቀቴ ባሰ።

መዝሙር 39