መዝሙር 37:9-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ክፉ ሰዎች ይጠፋሉና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ምድርን ይወርሳሉ።

10. ለአፍታ እንጂ፣ ክፉ ሰው አይዘልቅም፤ስፍራውንም ብታስስ አታገኘውም።

11. ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤በታላቅ ሰላምም ሐሤት ያደርጋሉ።

12. ክፉዎች በጻድቃን ላይ ያሤራሉ፤ጥርሳቸውንም ያፋጩባቸዋል።

13. እግዚአብሔር ግን ይሥቅባቸዋል፤ቀናቸው እንደ ደረሰ ያውቃልና።

መዝሙር 37