መዝሙር 37:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤መንገዱ በተቃናለት፣ክፋትንም በሚሸርብ ሰው ልብህ አይሸበር።

8. ከንዴት ተቈጠብ፤ ቍጣንም ተወው፤ወደ እኵይ ተግባር እንዳይመራህ አትከፋ።

9. ክፉ ሰዎች ይጠፋሉና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ምድርን ይወርሳሉ።

10. ለአፍታ እንጂ፣ ክፉ ሰው አይዘልቅም፤ስፍራውንም ብታስስ አታገኘውም።

11. ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤በታላቅ ሰላምም ሐሤት ያደርጋሉ።

መዝሙር 37