መዝሙር 37:27-36 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. ከክፉ ራቅ፤ መልካሙንም አድርግ፤ለዘላለምም ትኖራለህ።

28. እግዚአብሔር ፍትሕን ይወዳልና፤ታማኞቹንም አይጥልም፤ለዘላለምም ይጠብቃቸዋል፤የኀጢአተኛው ዘር ግን ይጠፋል።

29. ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤በእርሷም ለዘላለም ይኖራሉ።

30. የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤አንደበቱም ፍትሐዊ ነገር ያወራል።

31. የአምላኩ ሕግ በልቡ አለ፤አካሄዱም አይወላገድም።

32. ክፉዎች ጻድቁን ይከታተሉታል፤ሊገድሉትም ይሻሉ።

33. እግዚአብሔር ግን በእጃቸው አይጥለውም፤ፍርድ ፊት ሲቀርብም አሳልፎ አይሰጠውም።

34. እግዚአብሔርን ደጅ ጥና፤መንገዱንም ጠብቅ፤ምድሪቱን ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ክፉዎችም ሲጠፉ ታያለህ።

35. ክፉና ጨካኙን ሰው፣እንደ ሊባኖስ ዝግባ ለምልሞ አየሁት፤

36. ዳግመኛ በዚያ ሳልፍ፣ እነሆ፣ በቦታው አልነበረም፤ብፈልገውም አልተገኘም።

መዝሙር 37