መዝሙር 37:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ዐመፀኞችን በማየት አትሸበር፤በክፉ አድራጊዎችም አትቅና፤

2. እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፤እንደ ለምለም ቅጠልም ይጠወልጋሉ።

3. በእግዚአብሔር ታመን፤ መልካምንም አድርግ፤በምድሪቱ ተቀመጥ፤ ዘና ብለህ ተሰማራ።

4. በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።

5. መንገድህን ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤በእርሱ ታመን፤ እርሱም ያከናውንልሃል፤

መዝሙር 37