መዝሙር 33:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ጻድቃን ሆይ፤ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ቅኖች ሊወድሱት ይገባቸዋል።

2. እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፤ዐሥር አውታር ባለውም በገና ዘምሩለት።

3. አዲስ መዝሙር ዘምሩለት፤በገናውን ባማረ ቅኝት ደርድሩ፤ እልልም በሉ።

4. የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነውና፤የሚሠራውም ሁሉ የታመነ ነው።

መዝሙር 33