መዝሙር 22:19-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤አጋዤ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።

20. ነፍሴን ከሰይፍ ታደጋት፤ውድ ሕይወቴንም ከውሾች ጡጫ አድናት።

21. ከአንበሶች አፍ አድነኝ፤ከአውራሪስ ቀንድም ታደገኝ።

22. ስምህን ለወንድሞቼ እነግራለሁ፤በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ።

23. እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ፤አወድሱት፤እናንተ የያቆብ ዘር ሁላችሁ፤ አክብሩት፤የእስራኤልም ዘር ሁላችሁ፤ እርሱን ፍሩት።

መዝሙር 22